የእግዚአብሔር ጦር ዕቃ

ኤፌሶን 6:10-18

10  
በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ።

11  
የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ።

12  
ምክንያቱም ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው።

13  
ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና።

14  
እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣

15  
በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ።

16  
ከእነዚህም ሁሉ ጋር፣ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤

17  
የመዳንን ራስ ቊር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

18  
በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ፤ ይህንም በማሰብ ንቁ፤ ስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ።

Ephesians 6 in Amharic

Ephesians 6 in English

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። 

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። 

4  
ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታ በይም፤

5  
ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፣ በደልን አይቈጥርም።

6  
ፍቅር ከእውነት ጋር እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

7  
ፍቅር ሁል ጊዜ ይታገሣል፤ ሁል ጊዜ ያምናል፤ ሁል ጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁል ጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

8  
ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።

9  
ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምን ናገረውም በከፊል ነው።

10  
ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል።

11  
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ።

12  
አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

13  
እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

1 Corinthians 13 in Amharic

1 Corinthians 13 in English