ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። 

ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። 

4  
ፍቅር ታጋሽ ነው፤ ደግሞም ቸር ነው። ፍቅር አይመቀኝም፤ አይመካም፤ አይታ በይም፤

5  
ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፣ በደልን አይቈጥርም።

6  
ፍቅር ከእውነት ጋር እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

7  
ፍቅር ሁል ጊዜ ይታገሣል፤ ሁል ጊዜ ያምናል፤ ሁል ጊዜ ተስፋ ያደርጋል፤ ሁል ጊዜ ጸንቶ ይቆማል።

8  
ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ነገር ግን ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ይሻራል።

9  
ምክንያቱም የምናውቀው በከፊል ነው፤ ትንቢት የምን ናገረውም በከፊል ነው።

10  
ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ በከፊል የነበረው ይሻራል።

11  
ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፤ እንደ ልጅ ዐስብ ነበር፤ እንደ ልጅም አሰላ ነበር። ከጐለመስሁ በኋላ ግን የልጅነትን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቻለሁ።

12  
አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።

13  
እንግዲህ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

1 Corinthians 13 in Amharic

1 Corinthians 13 in English

This post is also available in: ፖርቱጋልኛ አረብኛ ቤላሩሲያን ቤንጋሊ ቡልጋርያኛ ዳኒሽ ፊኒሽ ጆርጅያን ግሪክኛ ሂንዱ ሃንጋሪያን ማላይ ሞኒጎሊያን ኔፓሊ ኖርወይኛ ፖርቱጋልኛ (ፖርቱጋል) ሲንሃላ ስሎቫክ ስዋሕሊ ስዊድንኛ ታሚል ተሉጉ ቱርኪሽ ዙሉ ቼክ ማላያላም ስፓኒሽ (ስፔን) ሊቱኒያን ማራቲ ፐንጃቢ ጉጅራቲ መቂዶኒያ ኡዝቤክ

CategoriesUncategorized